ኣማርኛ

How to vote correctly in local council elections (Amharic)

Information in Amharic about voting in the 2020 local council elections that will be held by post in Victoria.
Transcript

ጤና ይስጥልኝ ስሜ ….... ይባላል። በቪክቶሪያ የምርጫ ኮሚሽን ውስጥ (የዴሞክራሲ አምባሳደር ሆኘ እየሰራሁ እገኛለሁ) ወይንም (ስራተኛ ነኝ)

ከነሐሴ 22 (ኦገስት 28) ከሰዓት በኋላ 4 ፒኤም በፊት በመራጮች መዝገብ ውስጥ ስምዎ ከተካተተ የድምጽ መስጫ ካርዱ ጥቅል በፖስታ ወደ መስከርም መጨርሻ (ኦክቶበር መጀመሪያ) አካባቢ ይደርስዎታል።

እስከ ጥቅምት 6 (ኦክቶበር 16) ባለው ጊዜ የድምጽ መስጫ ካርዱ ጥቅል ካልደርሰዎ እባክዎን ወደ 9209 0190 ስልክ ደውለው አዲስ ማግኘት ይችላሉ።

እስቲ የድምጽ መስጫ ካርዱ ጥቅል ውስጥ ምን እንዳለ እንይ  የድምጽ መስጫ ካርድ ከተመራጮች የምርጫ ቅስቀሳ ጽሁፍ ጋር

ባለ ብዙ ቋንቋ የድምጽ አሰጣጥ መመሪያ በራሪ ጽሁፍ

የምርጫ ካርድ ኢንቨሎፕ

ተመላሽ የተከፈለበትን ኢንቨሎፕ

 እንዴት አድርገው በትክክል እንደሚመርጡ ላሳይዎት።

አንደኛ  –  የድምጽ መስጫ ካርዱን ከተመራጮች የምርጫ ቅስቀሳ ጽሁፍ ይነጥሉት

ሁለተኛ  –  የሚያስፈልግዎ ከሆነ የተመራጮችን የምርጫ ቅስቀሳ ጽሁፍ በሌላ ሰው ያስነብቡት። ከዚያም በኋላ ማንን እንደሚመርጡ ይወስኑ።

ሶስተኛ  –  እንዴት አድርገው ነው በትክክል የሚመርጡት

እርስዎ በፈቀዱት ቅደም ተከተል መሰርት ሁሉም ሳጥኖች ውስጥ ቁጥር ያስቀምጡ።

ንዲያሸንፍ በሚፈልጉት ተወዳዳሪ ትይዪ ባለው ሳጥን ላይ 1ን ይጻፉ

ሁለተኛ ምርጫዎ በሆነው ተወዳዳሪ ትይዪ ባለው ሳጥን ላይ 2ን ይጻፉ

ሶስተኛ ምርጫዎ በሆነው ተወዳዳሪ ትይዪ ባለው ሳጥን ላይ 3ን ይጻፉ

ሁሉም ሳጥኖች ውስጥ የግድ ቁጥር መጻፍ አለብዎ

ተሞላውን የምርጫ ካርድ እንዴት እንደሚመልሱ ላሳይዎ።

አንደኛየሞሉትን የምርጫ ካርድ በምርጫ ካርድ ኢንቨሎፕ ውስጥ ያስገቡ

ሁለተኛበምርጫ ካርድ ኢንቨሎፑ ጀርባ ላይ ፊርማዎትን፣ የትውልድ ዘመንዎን እና ቀኑን ካሰፈሩ በኋላ ኢንቨሎፑን ያሽጉት

ሶስተኛየታሸገውን የምርጫ ካርድ ኢንቨሎፕ ተመላሽ በተከፈለበት ኢንቨሎፕ ውስጥ ያስገቡት

አራተኛተመላሽ የተከፈለበትን ኢንቨሎፕ በተቻለ ፍጥነት ከዓርብ ጥቅምት 13 (ኦክቶበር 23) ከሰአት በኋላ 6 ፒኤም በፊት በፖስታ ቤት ውስጥ እንዲሆን ያድርጉ ወይንም እርስዎ አካባቢዎ ወደሚገኘው የምርጫ ጣቢያ ይውሰዱት።

የአካባቢ ምክር ቤትዎ። የእርስዎ ምርጫ። 

ጥቅምት 2013

ጥቅምት 2013 (ክቶበር 2020) ስለሚካሄደው የአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) ምርጫ

የአካባቢ ምክር ቤት ምርጫ የሚካሄደው ጥቅምት (ኦክቶበር) ነው። እቤትዎ ሆነው ለመምርጥ የሚያስችልዎት የምርጫ ካርድ ይላክልዎታል፡፡

በካሲ ከተማ ምክር ቤት፣ በሳውዝ ጊብስላንድ ሻየር አካባቢ ምክር ቤት እና በዊትለሲያ ከተማ ምክር ቤቶች ምርጫ አይደርግም። በነዚህ ሶስት የአካባቢ ምክር ቤቶች ያሉ ድምጽ ሰጭዎች ድምጽ መስጠት አያስፈልጋቸውም።

ድምጽ ለመስጠት እንዲችሉ ድምጽ ሰጪዎች እስከ ዓርብ ነሐሴ 22 2012 (ኦገስት 28 2020) ከሰዓት በኋላ 4 ፒኤም ድርስ መመዝገብ አለባቸው። የድምጽ መስጫ ካርዱ ለመራጮች በፖስታ  ከመስከርም  26 እስከ 28 2013 (ኦክቶበር 6 እስከ 8 2020)  ባለው ጊዜ ይላካል።

የርስዎን ድምጽ መስጫ ካርድ  በተቻለ ፍጥነት ከሞሉ በኋላ ምርጫው ከሚጠናቀቅበት ከዓርብ ጥቅምት 13 (ኦክቶበር 23) ከሰአት በኋላ 6 ፒኤም  በፊት ይመልሱ። 

ማነው ለመምርጥ መመዝገብ ያለበት?

በአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) ምርጫ ላይ ሁለት ዓይነት የምርጫ ምዝገባዎች አሉ: እነኝህም የክልል እና የአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) ምዝገባ ናቸው።

ለክልል ምርጫ  የተመዘገቡ  መራጮች

በክልል ምርጫ መዝገብ ላይ ስምዎ ካለ በጥቅምት (ኦክቶበር) ላይ በሚካሄደው የአካባቢ ምክር ቤት ምርጫ መዝገብ ላይ ስምዎ ይኖራል።

በክልል ምርጫ መዝገብ  ላይ ለመመዝገብ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለብዎ  የአውስትራሊያ ዜግነት፣ በምርጫው ቀን  (ቅዳሜ ጥቅምት 14 2013 ወይንም ኦክቶበር 24  2020) እድሜዎ 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ እና ቪክቶሪያ ውስጥ ቢያንስ ለአንድ ወር የኖሩ መሆን አለብዎ።

የአውስትራሊያ ዜጋ ከሆኑ እና በክልል ምርጫ መዝገብ  ላይ እንዳሉ ለማጣራት ከፈለጉ በዚህ ድረገጽ ላይ ‘የእኔን ምዝገባ  ሁኔታ ማጣራት/Check My Enrolment’ የሚለውን ይጫኑ ወይም ወደ እኛ በ 131 832 ላይ ይደውሉ። የአማርኛ አስተርጓሚ የሚፈልጉ ከሆነ  ወደ 03 9209 0190 መደወል ይችላሉ።

አውስትራሊያዊ ከሆኑ እና እድሜዎ 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ ከሆነ ለመምርጥ በአማርኛ የተተረጎመውን የመስመር ላይ (ኦንላይን) መመዝገቢያ ማመልከቻ ቅጽ እዚህ ገጽ ወደታች ያገኙታል።  የማመልከቻ ቅጹን በእንግሊዝኛ መሙላት አለብዎ ከዚያም  የማመልከቻ ቅጹን ሲያትሙበት በእንግሊዝኛ ይወጣል። ከዚያም በቅጹ ላይ ከፈርሙ በኋላ ወደሚከተለው አድራሻ  ይላኩት

Victorian Electoral Commission
Reply Paid 66506
Melbourne Vic 8001

ፖስታውን ሲልኩት በነጻ ነው፣ ቴምብር አያስፈልገውም።

ለመምርጥ የተመዘገቡ ሆነው ነገር ግን አድራሻዎን ቀይርው ወይንም ስምዎን ቀይርው ዝርዝርዎን ካላሻሻሉ፣ እዚህ ገጽ ወደታች ያለውን መገናኛ ተጠቅመው ዝርዝርዎን የመመዝገቢያ ቅጹን በመሙላት ወቅታዊ ያድርጉ።

ነሐሴ 22 (ኦገስት 28) ከሰዓት በኋላ ከ4 ፒኤም በፊት ለመምርጥ የተመዘገቡ ከሆነ ዝርዝር መረጃዎን ወቅታዊ ያድርጉ ወይንም ለመምርጥ ይመዝገቡ።

ነጻ የመራጮች ማንቂያ የስልክ መልእክት (ኤስኤምኤስ) ወይም በኢሜል የመራጮች ማስታወሻ እንዲደርስዎት  የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎን የሞባይል ስልክዎን ወይም የኢሜል አድራሻዎን በመመዝገቢያ ቅጹ ላይ ያካትቱ።

ለአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) ምርጫ የተመዘገቡ መራጮች

ለአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) ምርጫ የተመዘገቡ መራጮች  በምርጫው እለት (ቅዳሜ ጥቅምት 14 2013 ወይንም ኦክቶበር 24  2020) እድሜያቸው 18 ዓመት ወይም ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው እንዲሁም በክልል  ምክር ቤት የምርጫ መዝገብ ውስጥ የተካተቱ መሆን የለባቸውም።

ባለፈው የአካባቢ ምክር ቤት ምርጫ ሲካሄድ በመራጭነት የተመዘገቡት አሁን ከሚኖሩበት የአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) ውጭ ከሆነ፣ ጥቅምት(ኦክቶበር) ላይ በሚደርገው ምርጫ የምርጫ ካርዱ ቀድሞ ወደሚኖሩበት አድራሻ ይላክልዎታል።

የአውስትራሊያ ዜግነት ከሌለዎት ነገር ግን:

 • በአካባቢ ምክር ቤቱ (ካውንስሉ) ውስጥ እየኖሩ ግብር የሚከፍሉ ከሆነ ወይንም
 • በአካባቢ ምክር ቤቱ (ካውንስሉ) ውስጥ ግብር ከከፈሉ (ለምሳሌ፡ የተከራዩት ሱቅ ካለ) ነገር ግን በክልል ምክር ቤቱ ውስጥ ምንም ሌላ የመምርጥ መብት ከሌለዎ ወይም
 • ከሚኖሩበት የአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) ውጭ ንብረት ካለዎት ነገር ግን ባለፈው የአካባቢ ምክር ቤት ምርጫ የመራጮች መዝገብ ላይ ስምዎት ካልተካተተ።

በአካባቢዎ ምክር ቤት (ካውንስል) ምርጫ ላይ ለመምርጥ ወደ አካባቢ ምክር ቤቱ ማመልከት ይችላሉ።. የመመዝገቢያ ቅጽን ለማግኘት ወይም በአካባቢ ምክር ቤቱ የተመዘገቡ መራጭ መሆንዎትን  ለማጣራት የአካባቢዎን ምክር ቤት ማነጋገር ያስፈልግዎታል።

በአካባቢ  ምክር ቤት (ካውንስል) ምርጫ እንዴት ነው ምመርጠው?

የድምጽ መስጫ ካርዱ በፖስታ ከመስከርም 26 እስከ 28 2013 (ኦክቶበር 6 እስከ 8 2020) ባለው ጊዜ ይላክልዎታል።

የድምጽ መስጫ ካርዱን የያዘውን ፖስታ ሲከፍቱ የሚከተሉትን ያገኛሉ:

 • ከተመራጮች የምርጫ ቅስቀሳ በራሪ ጽሁፍ እና ፎቶግራፍ ጋር የተያያዘ የድምጽ መስጫ ካርድ።
 • የድምጽ አሰጣጥ መመሪያ (የተተርጎመ)
 • ማሸጊያ ያለው የድምጽ መስጫ ካርድ ፖስታ
 • ተመላሽ የተከፈለበት ፖስታ

እንዴት ነው ምመርጠው

 • እንዲያሸንፍ በሚፈልጉት ተወዳዳሪ ትይዪ ባለው ሳጥን ላይ 1ን ይጻፉ
 • ሁለተኛ ምርጫዎ በሆነው ተወዳዳሪ ትይዪ ባለው ሳጥን ላይ 2ን ይጻፉ
 • ሁሉም ሳጥኖች ቁጥር እስኪኖራቸው ድረስ ይቀጥሉ
 • ቁጥሮችን ብቻ ይጠቀሙ

የሜልበርን ከተማ ምክር ቤት (ሲቲ ካውንስል)  ለየት ያለ የምርጫ ደንብ አለው። በሜልበርን ከተማ ምክር ቤት  (ሲቲ ካውንስል)  ለመምርጥ የተመዘገቡ ከሆነ  ሁለት የምርጫ ካርዶች ይደርሱዎታል።

ትንሹ የምርጫ ካርድ የከተማ ምክር ቤቱን (ሲቲ ካውንስሉን) ከንቲባ እና ምክትል ከንቲባ ለመምርጥ ሲሆን እንደ ምርጫዎ ቅደም ተከተል በሁሉም ሳጥኖች ውስጥ ቁጥር ማስፈር አለብዎ።

ትልቁ የምርጫ ካርድ የከተማ ምክር ቤቱን (ሲቲ ካውንስሉን) አባላት ለመምርጥ ነው። እርስዎ መምረጥ ለፈለጉት የመማክርቶች ቡድን ‘1’ን ከመስመር በላይ በመጻፍ ድምጽ መስጠት ይችላሉ።

ወይም

ከመስመር በታች ባሉት ሳጥኖች ውስጥ ለእያንዳንዱ የከተማ ምክር ቤት (ሲቲ ካውንስል) ተመራጭ ቁጥሮችን በመጻፍ ድምጽ መስጠት ይችላሉ። ከመስመር በታች ድምጽ የሚሰጡ ከሆነ፤ ከመስመር በታች በያንዳንዱ ሳጥን ላይ እንደምርጫዎ በቅድመ ተከተል ቁጥር መስጠት አለብዎ።

ድምጽ መስጠቱን ካጠናቀኩ በኋላ ምን ማድርግ አለብኝ? 

 1. የሞሉዋቸውን የምርጫ ካርድ/ዶች የምርጫ ካርድ ፖስታ (ባለ ክዳን ፖስታ) ውስጥ ካስገfቡዋቸው በኋላ ማሸግ።
 2. በምርጫ ካርድ ፖስታ ክዳን ላይ የርስዎን ዝርዝር መረጃ ይሙሉ
 3. ወደ እኛ ከመላክዎ በፊት የታሸገውን የምርጫ ካርድ ፖስታ ተመላሽ በተከፈለበት ፖስታ ውስጥ ያስገቡት።

የርስዎን ድምጽ መስጫ ካርድ በተቻለ ፍጥነት ከሞሉ በኋላ ምርጫው ከሚጠናቀቅበት ከዓርብ ጥቅምት 13 (ኦክቶበር 23) ከሰአት በኋላ 6 ፒኤም በፊት ይመልሱ። 

ለአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) መወዳደር ከፈለጉ

ጥቅምት (ኦክቶበር) ውስጥ በሚካሄደው የአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) ምርጫ ላይ ለመወዳደር ከፈለጉ ደንቦችን መረዳት ይኖርብዎታል።  ይህን እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ የበለጠ መረጃ ማግኘት ከፈለጉ እባክዎን  በስልክ 131 832 ወደ እኛ ይደውሉ ወይም በአማርኛ አስተርጓሚ መስመር ስልክ 03 9209 0190 ላይ ይደውሉ።

በምርጫው ላይ መሥራት

የቪክቶሪያ ምርጫ ኮሚሽን ከሁሉም የቋንቋ ማህበርሰቦች የተወጣጡ ሰዎች በምርጫ ጊዜ እንዲሰሩ ለመቅጠር ይፈልጋል። ፍላጎት ካለዎት እባክዎን በሚከተለው ድረ ገጽ ማመልከቻውን በእንግሊዝኛ ይሙሉ https://appointments.vec.vic.gov.au/

አንዴ ከተመዘገቡ በኋላ ስራ ይሰጥዎታል ብለን መተማመኛ ልንሰጥዎ  አንችልም – ብዙ ነገሮች ግምት ውስጥ ይገባሉ ማለትም እንደ በየትኛው መስክ ወይም እንቅስቃሴ ላይ እርዳታ እንደሚያስፈልግ ማወቅ። በክልል ምርጫ ላይ ብዙ ሰዎችን እንፈልጋለን። የአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) ምርጫዎች በፖስታ ስለሚካሄዱ ብዙ ሰዎችን አንፈልግም።.

መምርጥ  ግዴታ ነው?

ለመምርጥ ለተመዘገቡ አውስትራሊያዊያን እንዲሁም በሜልበርን ከተማ ምክር ቤት (ሲቲ ካውንስል) ለመምርጥ ለተመዘገቡ ሁሉም መራጮች መምርጥ  ግዴታው ነው።

በአካባቢ ምክር ቤት (ካውንስል) የተመዘገቡ መራጭ ከሆኑ መምረጥ ግዴታ አይደለም።

ደህንነታቸው የተጠበቁ ምርጫዎችን ማካሄድ

መራጮችን፤ ተመራጮችን እና የቪክቶሪያ ምርጫ ኮሚሽን ሰራተኞችን ከኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) በሽታ ለመጠበቅ አስፈላጊውን እቅድ እያዘጋጀን ነው። ጥብቅ ጽዳት እና አካላዊ መራራቅ በሁሉም ቢሮዎች ውስጥ ተግባራዊ ይሆናሉ።

መምርጡን  ከረሳሁት ምን ይፈጠራል?

ያልመርጡበትን ምክንያት እንዲያስረዱ የሚጠይቅ ደብዳቤ ይደርስዎታል። እባክዎን ያልመርጡበትን ምክንያት ደብዳቤው ላይ ባለው ቦታ ላይ ይግለጹልን። ያቀርቡት ምክንያት ተቀባይነት ካላገኘ  የገንዘብ ቅጣት ሊጣልብዎ  ይችላሉ።

ጥያቄዎች አለዎት?

ስለዚህ መረጃ ጥያቄ ካለዎት እና እኛን በአማርኛ አስተርጓሚ ተርድተው ለማነጋገር ከፈለጉ ወደ  03 9209 0190 ይደውሉ።

 

እንዴት መምዝገብ ስለሚቻል

የመመዝገቢያ ቅጽ በእንግሊዝኛ (PDF, 2.0MB) መሙላት

የመመዝገቢያ ቅጹን በርስዎ ቋንቋ በድረገጽ ላይ ተጭኖ ማውጣት ነገር ግን ህትመት በእንግሊዝኛ ነው። ቅጹን የሚሞሉት በእንግሊዝኛ መሆን አለበት።